Loading...

Our Blog

Our Blog

Meseret Humaniterian

Heartfelt Thanks for Your Generous Donation and Visit

Image

Posted By: MHO

Dear Imam Hassen and team

On behalf of everyone at the Meseret Humanitarian Organization (MHO) Rehabilitation Center, I extend our deepest gratitude for your recent donation of food and your visit to our facility. Your kindness and generosity have left an indelible mark on our community, and we are profoundly grateful for your support.

Your donation of food comes at a critical time for us, as we strive to provide nutritious meals to the women and children under our care. Your contribution will not only nourish their bodies but also uplift their spirits, providing them with hope and encouragement during their journey towards rehabilitation and healing.

Your commitment to making a positive difference in the lives of others is truly inspiring. Your act of kindness serves as a beacon of hope, reminding us all of the power of compassion and solidarity. We are immensely grateful for your unwavering support and dedication to our cause.

Once again, thank you for your kindness, compassion, and generosity. We are deeply honored to have your support, and we look forward to the opportunity to welcome you back to our center in the future.

Special Thanks for our Taye Worku, for your continuous support and commitments

Together we can change many lives!

Image

Posted By: MHO

ተለውጠን የምንለውጥ ጠንካራ ሴቶች ነን!

የመልሶ ማቋቋም ስራ በመሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት አምቦ ቅርንጫፍ! በተለያዩ ምክንያቶች ለጎዳና ህይወት ተዳርገው የነበሩን 76 እናቶች ከነልጆቻቸው ከጎዳና በማንሳት እና በመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከላችን በማሰባሰብ ላለፋት 6 ወራት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ከሞራል ስብራታቸው አላቆ የእችላለሁ መንፈስ በማስታጠቅ የመልሶ ማቋቋም ስራውን ለእያንዳንዳቸው ቤት በመከራየት የቤት ዕቃ በማሟላት እና ሰርተው ራሳቸውን የሚያስችላቸውን ዕቃዎች በፍላጎታቸው ገዝቶ በመስጠት አቋቁሟል። እንኳን ደስስስ ያለን!

Image

Posted By: MHO

የፍቅር ስጦታ!

ደግነት አመስጋኝነት ለሌላ መትረፍ ካለ ማካፈል ተፈጥሯዊ ነው። እነዚህ የተለያዩ ምክንያቶች ጎዳና ያወጣቻቸው እናቶቾ በኛ በሰዋዊ መመዘኛ ምንም ለራሳቸው የልላቸው ቢመስሉንም ስብዕናቸው ሙሉ ለራሳቸው ባይኖራቸውም ለሌላ የሚሰጡት የማያጡ አመስጋኝ የደግ ልብ ባለቤቶች ናቸው። እጅግ በጣም ደስስስ ብሎኛል አመሰግናለሁ ። እናቶችዬ የሞላ የተረፈ ህይወት ይስጣችሁ! የሰለሞንን ጥበብ ይግለፅላችሁ! የምትሰጥት አትጡ!

Image

Posted By: MHO

ተለውጠን የምንለውጥ ጠንካራ ሴቶች ነን!

መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለያዩ ምክንያቶች ህይወት ወደ ጎዳና የጣለቻቸውን እናቶች ከነልጆቻቸው ከጎዳና በማንሳት የተለያዩ ስልጠናዎችን ሰጥቶ የ"እችላለሁ! " መንፈስ በማስታጠቅ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንዲጀምሩ መልሶ ያቋቁማል። በመሆኑም ላለፋት 5 ወራት በማዕከላችን ድጋፍና ስልጠና ሲሰጣቸው የነበሩት 174 እናቶች ከነልጆቻቸው እንደፍላጎታቸው ወደ ስራ የሚሰማሩበት የስራ መስሪያ ዕቃዎች ተበርክቶላቸዋል።

በዕለቱም ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ እና ከአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 7 የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት እናቶች የተሰማቸውን ደስታ እና የተማሩትን ትምህርት በተግባር በመተርጎም ከትንሽ ተነስተው እንዴት ወደትልቁ ግባቸው እንደሚደርሱ በሙዚቃዊ ድራማና በግጥም አስሰድተዋል።

በተጨማሪም የጎዳና ህይወት አስከፊነት ከዓላማዋ ያላናጠባት ዘንድሮ ከዩኒቨርስቲ በዲግሪ ለምትመረቀው የጥንካሬ ተምሳሌት እናት ለትምህርቷ ይረዳት ዘንድ የሞባይል ስጦታ ተበርክቶላታል።

ከአቃቂ ቃሊቲ ሴቶች ህፃናትና ሠራተኛና ማህበራዊ የመጡት አቶ ገብሩ ድርጅቱን ለሚሰራው መልካም ስራ አመስግነው ዛሬ ባዩት እጅግ እንደተደሰቱ ገልፀው እናቶች ራሳቸውንና ልጆቻቸውን መደገፍ እንዲችሉ በተሰጣቸው ድጋፍ ጠንክረው እንዲሰሩ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።

በተመሳሳይ ከወረዳ 7ሴቶች ህፃናት ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሃላፊ ወ/ሮ አስቴር እና ከቶ የቡድን መሪ የሆኑት አቶ ገለቱማ በተመሳሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከተባበርን ለሌላም እንተርፋለን!!!